በጅግጅጋ ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተመረቀ


ግንቦት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) በጅግጅጋ ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

በ250 ሚሊየን ብር ካፒታል የተከፈተው ፋብሪካው በቀን እስከ 10 መኪኖችን የመገጣጠም አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ፋብሪካውን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ይገኛል።

ፋብሪካው ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ጠቁመው የክልሉ መንግስትም ለግሉ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥል ብለዋል።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር ቅርንጫፍ)