በጉለሌ ክፍለ ከተማ አራት መጋዘን አለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ዋለ

የካቲት 28/2014 (ዋልታ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ አራት መጋዘን አለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በተቋቋመው ግብርኃይል በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
 
የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሰው ሰራሽ የዋጋ ውድነት በመፍጠርና ምርቶችን በመደበቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ህገወጥ ደላሎችንና ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግብርኃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ግብርኃይሉ እያደረገ ባለው ቁጥጥር በዛሬው እለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ ሙሉጌታ መናፈሻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኅብረተሰቡ ጥቆማ በአራት መጋዘን ውስጥ በርካታ መጠን ያለው የምግብ ዘይት ክምችት በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየሰራቸው ካሉ በርካታ ሥራዎች በተጨማሪ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብርኃይል በየአካባቢው ሰፊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡
ቁጥጥሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነና የከተማው ነዋሪም እንደተለመደው ጥቆማዎችን በማቅረብ የጋራ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡
 
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!