በጋይንት ግንባር የተደመሰሰው የሽብር ቡድን

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) በጋይንት ግንባር ደብረ ዘቢጥ አካባቢ መሽጐ የነበረው አሸባሪው ሕወሓት ከፍተኛ ሰብኣዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት ቦታውን እንደለቀቀ ተገለፀ።
ደብረዘቢጥ ከተማ ሙሉ በሙሉ ከአሸባሪ ቡድኑ ነጻ እንደሆነች የገለጹት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንደኛ ብርጌድ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን አሸባሪውን የማሸነፍ ሥራ አሁን በየአቅጣጫው በተጀመረው ስሜት ይቀጥላል ብለዋል።
በአካባቢው የነበረው ቡድን ወደ አግሪት አካባቢ እየሸሸ መሆኑንም ገልጸዋል። ቡድኑ አካባቢውን ትቶ ሲሸሽ የሞቱ አመራሮች አስከሬን እንዳይታወቅ አንገት እየቆረጠ መፈርጠጡንም አስታውቀዋል።
በታሪኳ መንግሥተአብ (ከጋይንት ግንባር)