በጌዴኦ ዞን ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) ብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ ባካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤ በመከረባቸው ውሳኔዎቸና አቋሞች ላይ የሚመክሩ የሕዝብ የውይይት መድረኮች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄዱ ነው፡፡
የጌዴኦ ዞንም የብልጽግና ፓርቲ ውሳኔዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የኢፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አስፋ (ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሠ መስተዳደር አወሉ አብዲ፣ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩ እንዲሁም የጌዴኦ ዞን በምክትል ማዕረግ ዋና አስተዳደሪ አብዮት ደምሴ ተገኝተዋል፡፡
የከተማ ነዋሪዎች ገንቢ ውይይት በማድረግ ለቀጣይ ብልጽግና ጉዞ የሚያግዙትን ሀሳቦችን በማመንጨት እንዲሁም በየደረጃ ያሉት አስፈፃሚ አካላት በዕቅድ በሚተገበሩ ጉዳዮች ላይ ገንቢ ውይይት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።
በመድረኩ በከተማው ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳይ ጽሑፍ በከተማው ከንቲባ ተስፋጽዮን ዳካ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡