በጎንደር ሲካሄድ የነበረው የሃይማኖት መሪዎች ጉባኤ ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

ግንቦት 02/2014 (ዋልታ) በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች በጎንደር ከተማ ሲካሄድ የነበረው በከፍተኛ የሃይማኖት መሪዎች ጉባኤ ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
ጉባኤው ባወጣው የአቋም መግለጫ ቀጣዮቹን 5 ነጥቦች አጽድቋል ።
1ኛ.  የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖቶች ለዘመናት የገነቡትን የእምነት እኩልነትንና የአብሮነት እሴት ጠብቆ ለመዝለቅ   ቃል እንገባለን፡፡
2ኛ.  የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖቶች ተከታዮችን ሽፋን በማድረግ የተፈፀመውን የወንጀል ድርጊት እናወግዛለን።
3ኛ.  በድርጊቱ ለተጎዱ ወገኖች መፅናናትን እንመኛለን፡፡ ድርጊቱ በድጋሚ እንዳይከሰት ኅብረተሰቡን በማስተባበር ለመስራት ቃል እንገባለን፡፡
4ኛ. በተፈፀው የፀጥታ ችግር የወደሙ ንብረቶችን በርብርብ ለመገንባት ቃል እንገባለን።
5ኛ. በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እጃቸው ያለባቸው ጥፋተኞች በሕግ እንዲጠየቁ በጋራ ለመስራት ቃል እንገባለን።
በውይይቱ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪዎች፣ የክልል የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ ከጎንደር ከተማ ከክርስትና እና ከእስልምና ሃይማኖት አባቶችና ተወካዮች፣ የሰላምና ልማት ሸንጎ የኮሚቴ አባላት እንዲሁም የበጎ አድራጎት ተሳታፊ ወገኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ መሆናቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡