ሰኔ 21/2013 (ዋልታ) – በጣሊያን በተደረገ ጄ ሶል ሙንላይት የግማሽ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል፡፡
በውድድሩ በወንዶች አትሌት ታዬ ግርማ 1 ሰዓት 4 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፣ አትሌት ዳምጤ ካሹ ታዬ 1 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ በመግባት 6ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል፡፡
በሴቶች ደግሞ አትሌት መሰረት እንግዱ አየለ 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት ማጠናቀቁን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡