በጣሊያን ኤምባሲ ላለፉት 30 ዓመታት ተጠልለው የቆዩት ተከሳሾች መለቀቃቸውን ተከትሎ የጣሊያን መንግስት አድናቆቱን ገለፀ

በጣሊያን ኤምባሲ ላለፉት 30 ዓመታት ተጠልለው የቆዩት ተከሳሾች ካሉበት የተከለለ ውስን ስፍራ መለቀቃቸውን ተከትሎ የጣሊያን መንግስት አድናቆቱን ገለፀ፡፡

በጣሊያን ኤምባሲ ላለፉት 30 ዓመታት ተጠልለው የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህና ሌተናል ጄኔራል አዲስ ተድላ ተጠልለው ካሉበት የተከለለ ውስን ስፍራ መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ኢማኑላ ክላውዲያ ዴል ሪ ለኢትዮጵያ መንግስት  ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሯ ጣሊያን በየትኛውም ቦታ እና በማንኛውም ጊዜ የሞት ቅጣትን አትቀበልም  ያሉ ሲሆን በርግጠኝነት አንድ የድሮ የታሪክ ገፅ ተቀይሯልም ብለዋል፡፡

እንዲሁም ጣልያን  እና ኢትዮጵያ ረጅም እና የበለፀገ መንገድን በጋራ ይጓዛሉ ማለታቸውን ከሚኒስትሯ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡