በጭና የንፁሃን ጭፍጨፋ የአፋር ክልል ሃዘን መግለጫ

ጳጉሜ 4/2013 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በአማራ ክልል ጭና ቀበሌ ባደረሰው የዘር ማጥፋት በተገደሉ ንፁሃን ዜጎች የተሰውን ሃዘን የአፋር ክልል መንግሥት ገለጸ፡፡

አሸባሪው ሕወሀት ንፁሃንን ማሸበር እና የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈፀም ዋና ተግባሩ አድርጎት ካሁን በፊት በአፋር ክልል ጋሊኮማ እና በተለያዩ አካባቢዎች እንዳደረገው በአማራ ክልልም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ በርካታ ንፁሀንን ጨፍጭፏል ብለዋል።

ቡድኑ በተለያዩ ግንባሮች ሽንፈትን እያስተናገደ ቢሆንም ንፁሃን ህፃናት፣ ሽማግሌዎችና ሴቶችን ሰለባ ያደረገ የዘር ማጥፋት በመፈፀም አረመኔያዊነቱን እና ኢሰብኣዊነቱን በተደጋጋሚ በተለያዩ ቦታዎች እያሳየ ይገኛል፣ በጭና ቀበሌ የተፈፀመው ጭፈጨፋ አንድኛው ነው ብሏል መግለጫው።

“በመጨረሻም በጭፍጨፋው ህይወታቸውን ላጡ ንፁሃን ዜጎች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለአማራ ክልል ሕዝብና ለመላው ኢትዮጵያዊያን መፅናናትን እንመኛለን” ብሏል፡፡