በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀድሞ አመራሮችና በአዲስ አመራሮች መካከል የስልጣን ርክክብ ተደረገ

ጥር 15/2015 (ዋልታ) የቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ስልጣናቸውን አስረክበዋል።

በርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የቀድሞ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡

የመጀመሪያዋ ሴት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ለማገልገል ለተሰጣቸው እድል ያመሰገኑት መዓዛ አሸናፊ ባለፉት 4 ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን በማስታወስ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

አዲሱ ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው የፍትህ አስተዳደር የሀገር ጉዳይ መሆኑን ገልጸው የፍርድ ቤት ነፃነትን ለማረጋገጥ፣ ተጠያቂነት እና ግልጽነት ለማምጣት የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንጠይቃለን ብለዋል።

የፍርህ ሥርዓቱ ላይ የሚስተዋለው የአገልግሎት ፍላጎት እና አቅርቦት ለማጥበብ አዲሱ አመራር እንደሚሰራም ገልፀዋል።

በትዕግስት ዘላለም