በፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ሀዋሳ ገባ

ሰኔ 21/2014 (ዋልታ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ የልዑካን ቡድን ሀዋሳ ገባ፡፡

የልዑካን ቡድኑ በብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ ለመገኘት ሀዋሳ መግባቱን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሀዋሳ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት መሰረት መስቀሌ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ እና ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድረገዋል፡፡