ሰኔ 08/ 2013 (ዋልታ) – በፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሚመራዉ በወደፊቱ የትምህርት ስርዓት ላይ የሚሰራው ዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርዓት ኮሚሽን ውይይት አካሄደ።
የወደፊቱ ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለማቀድ የተቋቋመው ኮሚሽን ሪፖርቱን ለማጠናቀቅ ከሁለተ ወር ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል ተብሏል፡፡
የኮሚሽኑ አባላት በሪፖርቱ ዝርዝር ይዘት ላይ የተወያዩበት ቁልፍ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡
ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ታዋቂ ባለሙያዎችን ያቀፈ ሲሆን ይፋዊ ክርክር፣ የፖሊሲ ውይይት ፣ የጋራ እርመጃዎችን የማያነሳሳ እና የትምህርት የወደፊት እጣ ፈንታ ምን መምሰል አለበት ለሚለዉ ዉይይት በር ከፋች የሚሆን ሪፖርት እያዘጋጀ ይገኛል ሲል የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
ሪፖርቱ ለዩኔስኮ ጠቅላላ ጉባኤ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2021 ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል፡፡