ባለፉት 10 ወራት ከ20 ሺሕ በላይ ግብር ከፋዮች የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ዘዴ መጠቀማቸው ተገለጸ

ግንቦት 9/2015 (ዋልታ) ባለፉት 10 ወራት ከ20 ሺሕ በላይ ግብር ከፋዮች የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ዘዴን በመጠቀም ከ61 ቢሊየን ብር በላይ መክፈላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የገቢ ሂሳቦች ዳይሬክቶሬት ገቢ ሂሳቦች ማጠቃለያ ቡድን አስተባባሪ ኤልሳቤጥ አሸናፊ ግብራቸውን ከከፈሉ 20 ሺሕ 772 ግብር ከፋዮች ውስጥ 8 ሺሕ 56 ግብር ከፋዮች በዘንድሮ የበጀት ዓመት የተመዘገቡ ግብር ከፋዮች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህ የክፍያ ዘዴም ባለፉት 10 ወራት ውስጥ 61 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብስሰብ መቻሉንም አመላክተዋል፡፡

ሥርዓቱ ግብር ከፋዮች ከአላስፈላጊ የገንዘብና የጊዜ ብክነት ተላቀው በቀላሉ ግዴታቸውን እንዲወጡ ያስቻለ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ መክፈያ ሥርዓት ከተዘረጋበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ከ22 ሺሕ በላይ ግብር ከፋዮች በአዲሱ የክፍያ ዘዴ የከፈሉ ሲሆን 127 ቢሊየን ብር ባለይ ተሰብስቧል መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡