ባለፉት 6 ወራት የ21 የመንገድ ፕሮጀክቶች የኮንትራት ውል ተፈረመ

በ2013 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት የ21 የመንገድ ፕሮጀክቶች የኮንትራት ውል ስምምነት ተፈርሟል።

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በሀገሪቱ የሚገኙ ነባር መንገዶችን ይዞታ ለማሻሻል እንዲሁም የስርጭት አድማሱን ከማስፋፋት አኳያ በእቅድ የተያዙ የ21 የመንገድ ፕሮጀክቶች የኮንትራት ውል ስምምነት ከሀገር በቀልና ከውጭ የስራ ተቋራጮች ጋር ተፈርሟል።

በየኮንትራቶቹ የውል ስምምነት መርሃ ግብር ላይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

የግንባታ ፕሮጀክቶቹን ለማከናወን የውል ፊርማው የተካሄደው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ እና የመንገድ ግንባታውን ጨረታ ካሸነፉት ሀገር በቀልና የውጪ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ጋር መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገድ ባለስልጣን የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።