ባለፉት ዓመታት መንግስት የፀጥታ መዋቅር ሪሮርሞች ሲያካሂድ ቆይቷል – የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ

መጋቢት 29/2015 (ዋልታ) ባለፉት ዓመታት መንግስት የፀጥታ መዋቅር ሪሮርሞችን ሲያካሂድ መቆየቱን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም መንግስት ባለፉት ዓመታት መንግስት የፀጥታ መዋቅሩን ለማሻሻል በርካታ ተግበራት እያከናወነ መቆየቱን ገልጸዋል።

ያለጠንካራ መከላከያ ሰራዊት ጠንካራ ሀገር መገንባት አይቻልም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የሪፎርም ስራውን መነሻ በማድረግ ጠንካራ ሰራዊት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የክልል ልዩ ኃይሎች ወደ ተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች እንዲካተቱ በጥናት ተቀምጧል ብለዋል።

በህልውናው ዘመቻ ምክንያት በጥናት ላይ የተመሰረተው ውሳኔ ወደ ተግባር ሳይገባ መቆየቱን አንስተው በመሆኑም አንድ ጠንካራ የተማከለ ሰራዊት መገንባት የሚያግዘው የጥናት ሂደት በመሆኑ የክልል ልዩ ኃይሎችን አሁን አንፃራዊ ሰላም መኖሩን ተከትሎ ወደ ተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች የማካተት ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡ ይህም ተግባር በሁሉም ክልሎች የሚተገበር ነው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት ልዩ ኃይሎች ሲያበረክቱ የነበረውን አስተዋፅአኦ መንግስት ሲያመሰግን ቆይቷል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ አሁንም እያመሰገነ የልዩ ኃይሉ በመከላከያ፣ በፌደራል አልያም በክልል ፖሊሶች መካተት የሚችሉበት አካሄድ መዘርጋቱን ጠቁመዋል።

መንግስት ይህ ጥናት ሲፈፅም በከፍተኛ ጥንቃቄ መሆኑን ነው በመግለጫው የተመለከተው።

በሰለሞን በየነ