ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ይከበራል

ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን  ”በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማ  ከፍታ”  በሚል መሪ ቃል ዛሬ ይከበራል።

ሰንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፣ የአንድ አገር ዜጎች  አገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜትን የሚገልፁበት፣ ታሪካዊ ትስስርና  ስነ-ልቦናዊ አንድነት  የሚንፀበረቁበት የአገራዊ አንድነትና ህብረት አርማና ምልክት ነው።

በመሆኑም ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር በህግ ተደንግጓል።

በዓሉ ዛሬ ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት በፌዴራል፣ በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ም/ቤቶች ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል እና  በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።