ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ሜቀዶኒያን ጎበኙ

ሰኔ 17/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ቡፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የሜቀዶኒያ የአረጋዊያን የአምዕሮ ህሙማን ማዕከልን ጎበኙ።
ፓትሪያሪኩ ከጠቅላይ ቤተ ክህነትና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ሌሎች አበው ሊቃነጳጳሳት እንዲሁም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች ጋር በመሆን ከ7 ሺሕ በላይ አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማንን የሚያስተዳድረው የሜቀዶኒያን ማዕከል በመጎብኘት ቡራኬና ፀሎት አድርገዋል።
ማዕከሉ በሦስ ዓመት ጊዜ 20 ሺሕ ተገልጋዮች ወደ ማዕከሉ ለማስገባት እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
በቅርቡም ሻሸመኔ፣ ደሴ፣ አምቦ፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ሃዋሳ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሆሳና፣ አርባ ምንጭ፣ አሶሳ ፣ ጅግጅጋ እና ሰመራ ከተሞች የአረጋዊያንና የአምዕሮ ህሙማን ማዕከል ለማስጀመር እየተንቀሳቀሴ ይገኛል።
በምንይሉ ደስይበለው