ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከሰሞኑ የደረሰውን የንጹሃን ግድያ አወገዙ

ሰኔ 16/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በወለጋና በጋምቤላ በደረሰውን አሰቃቂ የንጹሃን ግድያ ማዘናቸውን ገለጹ፡፡

ብፁዕነታቸው በመልዕክታቸው በወለጋና በጋምቤላ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ያወገዙ ሲሆን መንግሥትና ሕዝብ ግፍን በተግባር ማውገዝ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን ስለ ሰላም አስፈላጊነት ማስተማር ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን ከኢኦቴቪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡