ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ታላቁ የረመዳን ወር ይቅር የምንባባልበት ነው አሉ

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ

መጋቢት 22/2014 (ዋልታ) ታላቁ የረመዳን ወር ይቅር የምንባባልበት መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ገለጹ፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ የታላቁ ረመዳንን ወር ፆም አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ረመዳን ሙስሊሞች ራሳቸውን ከምግብና ከመጠጥ ብቻ የሚያርቁበት ወር ሳይሆን ራሳቸውን ከአላህ ጋር የሚያቀራርቡበትና የግል ስሜታቸውን እና ራስ ወዳድነታቸውን የሚያርቁበት ወር ነው ብለዋል።

ረመዳን ሸይጣን የታሰረበትና ቁርዓን የወረደበት እንዲሁም ይቅር የሚባባሉበት፣ ከ11 ወር ስህተታችን ወጥተን ወደ አላህ የምንቃረብበት እና ያለው ለሌለው አካፍሎ የሚያበላበት የረህመት ወር መሆኑን መጥቀሳቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

በመሆኑም ሙስሊሞች በዚህ የተቀደሰ ወር ተጠቃሚ እንድንሆን ራሳችንን ማስተካከል ይጠበቅብናል ብለዋል።

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!