ቱርክና ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የተመራ ልዑክ ቡድን በቱርክ ኢስታምቡል በመገኘት ከቱርክ ቢዝነስ ካውንስልና በሀገራችን በተለያዩ ኢንቨስትመንት መስኮች ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ የባንክ ዋስትና አሰጣጥ፣ የህግ ማስከበር ስራዎችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያሉ ክፍተቶች በውይይቱ ተሳታፊዎች ተነስተው በሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በቱርክ በኩልም በቀጣይ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፉ የበለጠ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መግለፃቸውን ከልዑኩ አባል እና በሚኒስቴሩ የንግድ ግንኙነትና ድርድር ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ምንዳዬ መግለጻቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡