ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ እውነታዎች

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ እውነታዎች

  • የግድቡ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለው፡- መጋቢት 24/2003 ዓ.ም በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አማካኝነት
  • የሚገኝበት ስፍራ፡- ግድቡ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባ ሲሆን፣ የሚገኘው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ ነው፡፡
  • ፕሮጀክቱ ያካተታቸው ሦስት ሥራዎች፡- የሲቪል ስራዎች ( civil works ) አሌክትሮ መካኒካል እና ሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸር ሥራዎች (Electromechanical & hydraulic steel structures ) እና ለግድቡ ስራ መኖሪያቸውን የለቀቁትን ሰዎች ማስፈርና ማቋቋም ናቸው፡፡
  • እንዲጠናቀቅ የታቀደለት ጊዜ፡- የግድቡ ስራ ሲጀመር በ6 ዓመት ጊዜ ውስጥ በ80 ቢሊዮን ብር ወጪ እንዲጠናቀቅ ታቅዶ ነበር፡፡
  • የህዳሴ ግድብ ሦስት አካላት

ዋነኛው ግድብ፡-145 ሜትር ከፍታ እና1780 ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡

ግድቡ ግራና ቀኝ የሚገኙት ሁለት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች፡-13 ተርባይን ጀነሬተሮችን ያካተቱ ሲኖን፣በአጠቃላይ5150 ሜጋዎች እና15760 ጃጋዋት ሰዓት በዓመት የማመንጨት አቅም አለው፡፡

የኮርቻ ግድብ (saddle Dam)፡-50ሜትር ቁመት እና 5200ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡

  • ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚይዘው የውሃ መጠን፡-74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ
  • ውሃው የሚተኛበት ስፍራ ስፋት፡-1874 ካሬ ኪሎ ሜትር ሲሆን ውሃው ከግድቡ ወደ ኋላ 240ኪሎ ሜትር ይረዝማል፡፡
  • የግድቡ ስራ በሚጠናቀቅበት ጊዜ ትልቅ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ይፈጠራል፡፡
  • የመልሶ ማቋቋም ስራ፡- ከግድቡ ግንባታ ጋርበተያያዘ፣የመኖሪያ ስፍራቸውን የቀየሩ 5390 አባወራዎችና እማወራዎችን መልሶ የማስፈር፣የማቋቋም እና የመሰረተልማት ግንባታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር የተያያዙ ያላላቅ ሁነቶች

  • ግንቦት 2005 የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ለመጀመሪያ ጌዜ ተቀየረ፡፡
  • መጋቢት 2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን መካከል የሶስትዮች የመርሆች ስምምነት ተፈረመ፡፡
  • ሃምሌ 2012 እና ነሀሴ 2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ የመጀመሪያ እነ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌቶችን አሳክታለች፡፡*
  • እስካሁን ለግድቡ ግንባታ ከ163 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ163 ቢሊዮን ብር ከሕዝባዊ መዋጮ የተገኘ ነው፡፡
  • የታላቁ ህዳሴ ግድብ ወጪ እስካሁን ሙለ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕዝብ የተሸፈነ ሲሆን በቀጣይነትም ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ ያጠናቅቁታል፡፡

 

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት