ትሕነግ አገር ለማፍረስ በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ ነው – ምርኮኛ ኮሎኔል ጉዕሽ ገብረ

ጥቅምት 25/2014 (ዋልታ) – አሸባሪው የትሕነግ ቡድን አገር የማፍረስ እቅዱን ለማሳካት በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሚገኝ በደሴ ግንባር የተማረከው የሽብር ቡድኑ ሜይዴይ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ጉዕሽ ገብረ ተናገረ።

የሽብር ቡድኑ በርካታ ህፃናትና ሽማግሌዎችን ያለ ትጥቅ በማሰለፍ ለአላስፈላጊ መስዋዕትነት እየዳረጋቸው እንደሚገኝም ምርኮኛው ተናግሯል።

ቡድኑ ሰሞኑን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ኃይል በማሰለፍ በደሴ ግንባር ውግያ ቢከፍትም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ሊደርስበት ችሏል።

እንደ ምርኮኛው ገለፃ የሽብር ቡድኑ ያሰማራው ኃይል ዲስፒሊን የሌለው በመሆኑ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ የግድያና ዘረፋ ተግባራትን አከናውኗል።

የሽብር ቡድኑ ያሰባሰበው የሰው ሃይል ብዛት ከታጠቀው የመሳሪያ ብዛት ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ አብዛኛውን የሰው ኃይሉን በባዶ ዕጅ በማሰለፍ የጥይት ሲሳይ እያደረገው እንእንደሚገኝ መናገሩን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።