ትውልዱ ታሪክ ሰሪ እንጂ ታሪክ አጥፊ መሆን የለበትም – የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ

ጥቅምት 14/2015 (ዋልታ) ትውልዱ ታሪክ ሰሪ እንጂ ታሪክ አጥፊ መሆን የለበትም ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ፒኤችዲ) ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በፎቶ አውደ ርዕይና በፓናል ውይይት እየተከበረ ባለውን የመከላከያ ቀን ላይ ባደረጉት ንግገር ነው፡፡
መርኃ ግብሩን የመክፈቻ በንግግር የከፈቱት የመከላከያ ሚኒስትሩ ቀኑ የመከላከያ ታሪክ የሚዘከርበት መሆኑን ገልጸው ትውልዱ ታሪክ ሰሪ እንጂ ታሪክ አጥፊ መሆን የለበትም ብለዋል።
ያለፉ ታሪኮች ጥሩ ይሁኑም መጥፎ የምንማርባቸው ለማንም የማንሰጣቸው ታሪኮቻችን ናቸው ብለዋል።
ተላላኪና አፍራሾ ኃይሎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከመዳፈራቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡ ያሳሰቡት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ጀግናና በዲስፕሊን የታነጸ ጠንካራና ዘመናዊ ሰራዊት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
ይህ ሀይል ማንም የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እንዳይደፍር የተከበረ ህይወቱን የሚሰጥ ጠንካራና ዘመናዊ ሰራዊት መሆኑን መስክረዋል፡፡
ኢትዮጵያን ለመድፈር የሚጥሩ ኃይሎች ዳግም እንዳያስቡት የሚያደርግ ሁለንተናዊ አቅም መፈጠሩንም ገልጸዋል።
በተስፋዬ አባተ