ሐምሌ 11/2013 (ዋልታ) – ከአምስት ሺሕ የሚበልጡ የአዲስ አበባ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሰራተኞች እና አንቀሳቃሶች ሃይሌ ጋርምንት አካባቢ 25 ሺሕ የሚጠጉ ችግኞችን ተከሉ፡፡
ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሀገር በቀል ችግኞች ናቸው ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በማህበረሰቡ ዘንድ ችግኝ የመትከል ባህሉ እያደገ ቢመጣም መንከባከብ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ መስራት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
የቢሮው ሰራተኞችና የአነስተኛና መካከለኛ ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችም የተከሏቸውን ችግኞች እንደሚንከባከቡ ቃል ገብተዋል፡፡
እንደሀገር የተጀመረውን ኢትዮጵያን በአረንጓዴ እጽዋት እናልብስ ሲሉ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማስጀመራቸው ይታወቃል።
ይህንን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ተብሏል፡፡
(በሳራ ስዩም)