አሁን እየጣለ ያለው ቀላል ዝናብ ለመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቆመ

ኅዳር 1/2015 (ዋልታ) በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት እየጣለ ያለው ቀላል ዝናብ ለመጪዎቹ ሦስትና አራት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን የበጋው ደረቅ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ፀባይ ተመልሶ የሚጠናከርበት ክስተት እንደሚፈጠር ኢንስቲትዩቱ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የአየር ሁኔታ እና የአየር ፀባይ ትንበያ ባለሙያ ታምሩ ከበደ ከዋልታ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሚጥለው ቀላል ዝናብ ታጭደው ባልተከመሩ ስብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል አርሶ አደሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

ዝናቡ ቀጣይነት ስለሌለው ዝናቡ ሲያቆም ጠብቆ ያልታጨዱ ሰብሎችን መሰብሰብ ይገባልም ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለውን የዝናብ አዝማሚያ ተከትሎ የሌሊት እና ማለዳው ቅዝቃዜ ጋብ እያለ እንደሚመጣም ባለሙያው አስታውቀዋል፡፡

በአሳየናቸው ክፍሌ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW