አመራሩ ሕዝቡን በታማኝነት እንዲያገለግል የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አሳሰቡ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) የክልሉ አመራር ሕዝብ የሰጠውን አደራ ጠብቆ በታማኝነት እንዲያገለግልና ኃላፊነቱን እንዲወጣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አሳሰቡ።
በክልሉ ባለፉት 3 ወራት የተከናወኑ ተግባራት በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ ተገምግመዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድሩ ሁሉም አመራር የተሰጠውን ኃላፊነት በታማኝነትና በብቃት መወጣት እንዳለበት ነው መመሪያ የሰጡት፡፡
በግምገማው የክልል፣ ዞንና ከተሞች የተሾሙ አዳዲስ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።