አሜሪካ ለአፋርና አማራ ክልሎች 250 ሜትሪክ ቶን የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

የካቲት 30/2014 (ዋልታ) የአሜሪካ መንግሥት በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በኩል በአፋርና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 250 ሜትሪክ ቶን የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ለክልሎቹ የተደረገው ድጋፍ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ግምት ያለው ምግብ ነክ ያልሆነ ቁሳቁስ ነው ተብሏል፡፡

ድጋፉ በአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንና በዓለም ዐቀፉ ስደተኞች ድርጅት በኩል ለተጎጂዎች እንደሚደርስ ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ድጋፉን በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነሲቡ ሁሴን ማስረከባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW