አሜሪካ አሸባሪው ሕወሓት በዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ላይ የፈፀመው ዝርፊያ አሳስቦኛል አለች

ነሐሴ 19/2014 (ዋልታ) አሜሪካ አሸባሪው ሕወሓት መቐሌ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ላይ የፈፀመው ዝርፊያ እንዳሳሰባት ገለጸች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ታጣቂ ቡድኑ ትናንት መቐሌ ወደሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በኃይል በመግባት 12 የነዳጅ ቦቴዎችን በአጠቃላይ 570 ሺሕ ሊትር ነዳጅ መዝረፉን ጠቁመው የነዳጅ ምርቱ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች የነብስ አድን ቁሳቁስ ለማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን አመላክቷል።

ለዜጎች የሚደረግ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን የሚከላከል ማናቸውንም ድርጊቶች አሜሪካ እንደምታወግዝ አስታውቋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW