አምባሳደር መለስ አለም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ

ሰኔ 16/2014 (ዋልታ) አምባሳደር መለስ አለም አምባሳደር ዲና ሙፍቲን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር መለስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ  ሆነው መሾማቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ደግሞ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው መሾማቸውም ተገልጿል፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ ማብራሪያ ከዓመታት በፊት ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡