አምባሳደር ስለሺ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቀረቡ

ሚያዝያ 28/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፕሮቶኮል ቺፍ ቢሮ አቅርበዋል።
አምባሳደር ስለሺ በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ያለውን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ለማጠናከር ከባልደረቦቻቸው ጋር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።