አምባሳደር ባጫ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ አቀረቡ

ሐምሌ 30/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ባጫ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ በኬንያ ቤተ መንግሥት ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ አቅርበዋል።

አምባሳደር ባጫ በዚሁ ወቅት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረውን የኢትዮ-ኬንያ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

አምባሳደር ባጫ ደበሌ በኬንያ 14ኛው የኢትዮጵያ አምባሳደር መሆናቸውን በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያሳያል።