አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎውኩክ ጋር ተወያዩ

መጋቢት 10/2013 (ዋልታ) – በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎውኩክ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች እንደተገመገሙ አምባሳደር ታዬ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ ምላሽ ለመስጠት በተሻለ ሁኔታ ድጋፍ ማሰባስበ እንደሚገባም በውይይቱ ወቅት አፅንኦት መሰጠቱንም አስታውቀዋል።