አምባሳደር አደም መሐመድ ከቱርክ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ጋር ተወያዩ

አምባሳደር አደም መሐመድ

ኅዳር 9/2015 (ዋልታ) በቱርክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሐመድ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ኤሊፍ ቾሞሉ ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደሩ በውይይታቸው ወቅት በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል ሰለተፈረመው የሰላም ስምምነት እና መንግስት ለሰላም ሂደቱ ያለውን ቁርጠኝት አስመልክቶ ለዳይሬክተር ጄኔራሏ ገለጻ አድርገዋል።

የቱርክ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አምባሳደር አደም በቀጣይ በሚከናወኑ ስራዎች ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ኤሊፍ በበኩላቸው በመንግስት እና በህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ እንዳስደሰታቸውና ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ከሰላም ስምምነቱ በተጨማሪ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW