አምቦ፣ ደምቢ ዶሎ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ

አምቦ፣ ደምቢ ዶሎ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠኗቸውን ተማሪዎችን አስመርቀዋል፡፡
አምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ5ሺህ በላይ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን እያስመረቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለተመራቂዎቹ በኮሮና ክስተት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት በማካካስ እንደተሰጣቸው እና ከተመራቂዎቹ መካከል 1ሺህ 810 ሴቶች መሆናቸው ተመልክቷል።
የምረቃው ሥነ-ሥርዓት በዩኒቨርሲቲው ሥር ባሉ ሃጫሉ፣ ጉደር ማሞ መዘምር፣ ወሊሶ ካምፓስና ዋናው ግቢ የሚያጠቃልል ነው።
የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ፣ በተለያዩ መርኃግብሮች ያሠለጠናቸውን 1 ሺህ 59 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ አስመርቋል።
በሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄደ ባለው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የፌደራልና ክልል ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡