የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 824 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት የምርቃት ስነ ስርዓት እያካሄደ ነው።
የኒቨርሲቲው ከአባያ፣ ከጫሞ፣ ከነጭ ሳር፣ ከሳውላ እና ከዋና ግቢ ካምፓስ በመደበኛ እና በኢ-መደበኛ መርሐግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ነው በዛሬው ዕለት እያስመረቀ የሚገኘው።
በዛሬው ዕለት እየተመረቁ ካሉት ተማሪዎች መካከል የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ይገኙበታል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ ጨምሮ የክልሉ እና የዞኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች በስነ ስርዓቱ ላይ ታድመዋል።
ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ የከፍተኛ ትምህርት ማእከል አቅም በማጎልበት ጥራት ባለው የትምህርት አሰጣጥ ለሀገር የሚበጁ እና በእውቀት የበለጸጉ ተማሪዎች በማበራከት ለሀገር ብልጽግና ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።