አርባምንጭ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ ሦስተኛ ተከታታይ ድል አስመዘገበ

ሰኔ 17/2014 (ዋልታ) በ28ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ዛሬ አርባምንጭ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና የፊት መሰመር አጥቂ አቡበከር ናስር ደማቅ ሽኝት በተደረገለት ጨዋታ ቡናማዎቹ ሽንፈት አስተናግደዋል፡፡
ለአርባምንጭ ከተማ የማሸንፊያው ብቸኛው ግብ ከመረብ ያሳረፈው አህመድ ሁሴን ነው፡፡
በመከላከል እና በመልሶ ማጥቃት የተጫወተው አርባምንጭ ከተማ ዛሬ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 41 በማድረስ 7ኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡
በዛሬ ጨዋታ ሽኝት የተደረገለት አቡበከር ናስር በቀጣይ የውድድር ዘመን ጀምሮ ለደቡብ አፍሪካው ማሚሎ ደ ሰንዳውንስ የሚጫወት ይሆናል፡፡
ሚኪያስ ምትኩ