አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በጎንደር አቀባበል ተደረገለት


ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ) –
ቴዲ አፍሮ በሰብዓዊ፣ በማኅበራዊና በጥበቡ ዘርፍ እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ ነገ በጎንደር ዩንቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ይበረከትለታል ብለዋል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን(ዶክተር)።
በቦታውም የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የከተማዋ ከንቲባ ሞላ መልካሙ እና የጎንደር የባሕል ማዕከል በጎንደር አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከአሚኮ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።