አሸባሪው ህውሓት በፈንቲ ረሱ ዞን ነዋሪዎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ፈጽሞብናል-አርብቶ አደሮች


ነሀሴ 3/2013 (ዋልታ)
-አሸባሪው ህውሓት በፈንቲ ረሱ ዞን ነዋሪዎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ፈጽሞብናል ሲሉ በዱብቲ ሆሲፒታል ህክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ንጽሃን አርብቶ አደሮች ገለጹ፡፡
ሽብርተኛው ህወሓት በለሊት በተኙበት በህጻናት፣ በሴቶች እና በአዛውንቶች ላይ አሳፋሪና ዘግናኝ ጭፍጨፋ መፈጸሙን አርብቶ አደሮቹ ገልጸዋል፡፡
የተደረገባቸው ጭፍጨፋ በአፋር ታሪክ ውሰጥ መቼም የማይረሳ መሆኑን የገለጹት አርብቶ አደሮቹ ፣የአፋር ህዝብ በኢትዮጵያዊቱ የማይደራደር ኩሩ ህዝብ ነው ብለዋል፡፡
የአፋር ህዝብ አይደለም ክልሉን ከውጭም ከውስጥም ኢትዮጵያን ለመውረር ሙከራ ያደረጉትን አሳፍሮ የመለሰ ጀግና ህዝብ መሆኑን ህክምና በመከታተል የሚገኙ ንጽሃን አርብቶ አደሮቹ መግለጻቸውን ከአፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡