አሸባሪው ሕወሓት የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብን አወደመ

ታኅሣሥ 1/2014 (ዋልታ) አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በኮምቦልቻ የሚገኘውን ደረቅ ወደብ ተርሚናል ላይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ዘረፋና ውድመት ማድረሱን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የኮምቦልቻ የደረቅ ወደብ ተርሚናል ከ251 በላይ የደንበኛ ንብረቶችን የያዙ ኮንቴይነሮች መዘረፋቸውን በድርጅቱ የወደብ እና ተርሚናል አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ምህረተአብ ተክሉ ገልጸዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ከዚህ ቀደም ሲያደርገው እንደነበረው ወደቡ ላይም የቻለውን በመዝረፍ ያልቻለውን ደግሞ ማውደሙን አስረድተዋል።

በተጨማሪም በደረቅ ወደቡ ንብረት የነበራቸውን ግለሰቦች በማግኘት እንደሚያነጋግሯቸው አቶ ምህረት መናገራቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡