አሸባሪው በመርሳ ድሬ ሮቃ መደምሰስ

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ድሬ ሮቃ አሸባሪውን ድባቅ እንደመታው የመከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።

በአፋር ክልል ሚሌ መስመርን ለመያዝ ቋምጦ በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ወረዳ ድሬ ሮቃ በተባለ አካባቢ በአራት አቅጣጫ ማለትም በጮቤ፣ በቀለንቲ፣ ሰርጢ እና ቀላ በተባሉ ተራሮችን ለመያዝ እና ሰብሮ ለመግባት የመጣውን አሸባሪ ኃይል ይዞት ከመጣው ሰውና ቁስ ጋር መደምሰሱን የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የአንድ ብርጌድ ዋና አዛዥ ተናግረዋል።

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይልና የክልል የፀጥታ ኃይሎች ሽብርተኛው ያደረጋቸውን ተደጋጋሚ ሙከራዎች በማክሸፍ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታልም ብለዋል።

“በዚህም 431 ተደምስሷል፤ 60 ክላሽ ፣ 3 ብሬን፣ 2 ስናይፐር እና 1 መገናኛ ሬዲዮ ተማርኳል” ነው ያሉት

በተለይ የአከባቢው ማህበረሰብ እና ታጣቂ ሰላሙን ነቅቶ ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ሰራዊቱ በተሳካ ሁኔታ በግዳጁ ድል እንዲያመጣ ትልቅ እገዛ ያደረገ ሲሆን ፣ በዚህም ምግብ ፣ ውሃ ፣ ተተኳሽ ሰራዊቱ እስካለበት ድርስ በማቅረብ እና አብሮነቱን በማጠናከር ለተገኘው ድል የአንበሳውን ድርሻ መያዙን የአንድ ብርጌድ ምክትል አዛዥ ተናግረዋል፡፡