አሸባሪውን ሕወሓት ወደተመኘው ሲኦል እንሸኛለን ሲል የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለፀ

ጥቅምት 28/2014 (ዋልታ) አሸባሪውን ሕወሓት ወደተመኘው ሲኦል በመሸኘት የኢትዮጵያን ነፃነት እናስጠብቃለን ሲል የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለፀ፡፡

በመስቀል አደባባይ አሸባሪዎቹን ሕወሓት እና ሸኔን የሚያወግዝና መከላከያ ሰራዊትን እንዲሁም ሌሎች የፀጥታ ኃይሎችን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሙሉጌታ አበበ ባስተላለፉት መልዕክት የክብራችን መገለጫ የሆነችውንና የመርከባችንን ኢትዮጵያን ሉኣላዊነት አናስደፍርም ብሏል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ከሁሉም ወገን አንድነት ኃይላችን፤ ኢትዮጵያዊነታችን ክብራችን ነው ብለን በመነሳት ጠላትን መደምሰስና ነፃነታችን ማስከበር አለብን ብለዋል፡፡

የፖለቲካ ልዩነትና ሥልጣን ከአገር በታች ነው ያሉት ሰብሳቢው አሸባሪውን ሕወሓት ወደተመኘው ሲኦል በመሸኘት የኢትዮጵያን ነፃነት ለማስጠበቅ የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡