አሸባሪዎችንና ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ተደረገ


ሚያዝያ 9/2014 (ዋልታ) የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት አሸባሪዎችንና ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ሰነድ ተፈራርመዋል።

የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት በድንበር፣ በሳይበር፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ዙርያ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በወጣቶችና ሥራ አጥነት በሌሎችም ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ነው የተስማሙት፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የወታደራዊ መረጃ ፎረም በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ታንዛኒያና ዩጋንዳ ተሳትፈዋል።

በቀጠናው ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ዙርያ ሲመከሩ የቆዩት የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት ኢትዮጵያ ለፎረሙ መሳካት ላደረገችው አሰተዋጾኦ አመስግነዋል።

የምክክር መድረኩ ከደኅንነት ጉዳዮች ባለፈ በዘርፉ የልምድ ልውውጥን ያካተተ ሲሆን የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤትን፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነትን እና የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት መስሪያ ቤቶችን ጎብኝተዋል።

መድረኩ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በትላንትናው ዕለት መካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል፤ ቀጣዩን የምክክር መድረክ ደግሞ ኡጋንዳ እንደምታዘጋጅ ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ይጠቁሟል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!