አብን የምርጫ ማኒፌስቶ ሰነዱን ይፋ አደረገ

ሚያዚያ 08/2013 (ዋልታ) – “ጠንካራና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንገነባለን” በሚል ሀሳብ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ ሰነዱን በዛሬው እለት ይፋ አደረገ።
ከተዋቀረ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠረው አብን በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚያራምደው ስርአት 220 ገፅ በያዘው ማኒፌስቶ ሰነድ በሶስት ምዕራፍ የተከፋፈለ መሆኑንም አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትስማማ የሁሉም ሀገር ሆና እንደምትቀጥል እምነታችን ነው በማለት የገለፁት የአብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ክርስትያን ታደለ ዘለቄታዊ ልማትና እድገት እናመጣለን ብለዋል።
ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን የሀገሪቱን ግብርና አብን ወደ ኢንደስትሪ መር በማሳደግ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል በማድረግ፣ በማልማት እና የተፈጥሮ ስጦታዎችን ከማስጠበቅ አንፃር እንደሚሰራ አቶ ክርስትያን አስታውቀዋል፡፡
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ግልፅ ተጠያቂ ብቁና ለህዝብ የቆመ አስተዳደር እንደሚዘረጋ ፅኑ እምነት እንዳለውም አስታውቋል።
(በሃኒ አበበ)
<img class=”j1lvzwm4″ src=”data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />