አትሌት ፀሃይ በሊዝበን ግማሽ ማራቶን አሸናፊ ሆነች

ግንቦት 2/2014 (ዋልታ) አትሌት ፀሃይ ገመቹ በሊዝበን ግማሽ ማራቶን ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፋለች፡፡

አትሌት ፀሃይ የሊዝበንን ግማሽ ማራቶን ርቀት 1 ሰዓት ከ 06 ደቂቃ ከ 44 ሴኮንድ በመግባት ነው ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀችው፡፡

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጎይቶም ገብረ ስላሴ 1 ሰዓት ከ07 ደቂቃ 11 ሴኮንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!