አቶ ታገሰ ጫፎ በድጋሚ የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባዔ ሆነው ተሾሙ

መስከረም 24/2013 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ የምስረታ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎን በድጋሚ የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባዔ በማድረግ ሾሟል፡፡

ምክር ቤቱ በ419 ድጋፍና በስድስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አቶ ታገሰ ጫፎን ዋና አፈ-ጉባዔ አድርጎ የሾመ ሲሆን ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡