አነስተኛና መካከለኛ አንተርፕራይዞች ለሀገር እድገት መሰረት ናቸው ተባለ

ግንቦት 13/2014 (ዋልታ) ተወዳዳሪ እና ሥራ ፈጣሪ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር ለሀገር ዕድገት መሠረት ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ይህን ያስታወቀው ካንኩ በወላይታ ሶዶ ከተማ ለ3ኛ ጊዜ ያዘጋጀውን ሀገር ዐቀፍ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ሲያጠናቅቅ ነው፡፡

በዕውቀት የተደገፈ ተወዳዳሪ እና ሥራ ፈጣሪ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር ለሀገር ዕድገት መሠረት በመሆኑ ለዘርፉ ሥራ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ባንኩ ጠቁሟል፡፡

ይህንኑ እውነታ በመረዳት ባንኩ በወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ለ4 ሺሕ 500 በላይ ሠልጣኞች ሥልጠና እንደተሰጠ የዲስትሪክቱ ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን ሳኦል ተናግረዋል።

ሥልጠናው ያተኮረው በቢዝነስ ጽንሰ ሀሳብ፣ በሂሳብ አስተዳደር፣ በንግድ ሥራ አመራር፣ በገበያ ትስስር እና የሰው ሀብት ኃይል አስተዳደር ላይ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ ስልጠናው ወጣቱን ስኬታማ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ከላይ በተጠቀሱት ርዕሶች ዙሪያ ስልጠናው ለአምስት ቀናት በአርባምንጭ ከተማ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW