አንዲት እናት ሦስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) በወላይታ ዞን ቦዲቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሦስት ወንድ ልጆችን በሰላም ተገላገለች።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ወልዴ ቡቃቶ እናቲት በሆስፒታሉ በቂ የቅድመ ወሊድ ህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደቆዩ ገልጸዋል።

በዚህም ዛሬ ረፋዱ ሦስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሦስት ልጆች በሰላም መገላገላቸውን አስታውቀዋል።

ወላዷ እናት በሰላም እንዲገላገሉ የህክምና ባለሙያዎች ላደረጉት ደጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ህፃናቱ የጤና ሁኔታቸው አሳሳቢ ባይሆንም ከሚጠበቀው ክብደት በታች በመሆናቸው ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ልዩ ሆስፒታል ለተሻለ ህክምና መወሰዳቸውም ተጠቁሟል፡፡

በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ የጊዶ ቦዲቲ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ብርሃነሽ ቆልቻ ከዚህ በፊት የወለዷቸው ሦስት ሴት ልጆች እንዳሏቸውም ለማወቅ ተችሏል።