አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ፀሐይ ሽፈራው

ሐምሌ 17/2016 (አዲስ ዋልታ) አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማገኘቱን አስታወቀ።

ባንኩ እ.አ.አ የ2023/2024 የሂሳብ አመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፀሐይ ሽፈራው የበጀት ዓመቱ መጠናቀቁን ተከትሎ አዋሽ ባንክ 11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መሰብሰብ መቻሉን ጠቅሰው በሌላ በኩል 37 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የተለያዩ አዳዲስ ብድሮች መስጠቱንም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 232 ቢሊዮን ብር ሲሆን የቅርንጫፎቹ ብዛት ደግሞ 947 መድረሱን አመላክተዋል።