አየር መንገዱ 36 ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ሊያስመጣ ነው

ጥቅምት 9/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ 36 አውሮፕላኖችን ለማስገባት ትዕዛዝ መስጠቱን አስታወቀ::

አየር መንገዱ ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ለማስገባት ምን ያህል ወጪ እንደሚያወጣ ያለው ነገር የለም፡፡

አየር መንገዱ እያደገ ከመጣው የደንበኞች ፍላጎት አንጻር ሁለት ቦይንግ 787 ድሪምላይነርን ጨምሮ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ሠላሳ ስድስት ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ለማስገባት ትዕዛዝ ሰጥቷል::

በአሁኑ ሰዓት አየር መንገዱ በዓለም ዙሪያ 130 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን የበረራ አውሮፕላኖች ቁጥርም ወደ 140 ደርሷል ።

ከአየር መንገዱ አሁን እያስተዳደራቸው ካሉ 140 አውሮፕላኖች ውስጥም 27 አውሮፕላኖች ቦይንግ 787 ድሪምላይነር መሆናቸው ታውቋል::