አየር መንገዱ ከኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን የበረራ ዕግድ ደብዳቤ እንደደረሰው አስታወቀ

ሐምሌ 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ወደ ኤርትራ የሚያደርጋቸውን ሁሉንም በረራዎች ማገዱን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደደረሰው አስታወቀ።

በፈረንጆቹ ሐምሌ 21/2024 የተጻፈ ደብዳቤ እንደደረሰው የገለጸው አየር መንገዱ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 30 ቀን 2024 ጀምሮ ወደ ኤርትራ የሚያደርጋቸውን ሁሉንም በረራዎች ማገዱን ይገልጻል ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳዩን አስመልክቶ የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ጉዳዩም በበጎ መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ያለውን ዕምነት ገልጿል።