ጥቅምት 20/2017(አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ወደ ቡርኪና ፋሶ ዋና ከተማ ኦጋዱጉ የዕቃ ጭነት በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።
በረራው ከጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጀምር የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።
አየር መንገዱ በአፍሪካ ውስጥ ዘመናዊ የጭነት ማመላለሻ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ከ60 በላይ በሚሆኑ የአህጉሪቱ ከተሞች እንደሚበር መረጃዎች ያመለክታሉ።